News Detail
Jan 30, 2023
3.7K views
#ማስታወቂያ የትምህርት ሚኒስቴር የምርምር ስነ ምግባር ግምገማን የተቀላጠፈ እና በተክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችል ድረ-ገፅ አዘጋጅቶ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ የተዘጋጀው ድረ-ገፅ ተመራማሪው ስራዎቹን ለማመልከት እንዲሁም ገምጋሚው ዶክመንቶቹን አይቶ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡
በመሆኑም የሚሰሩ የምርምር ስነ ምግባር ስራዎችን በተመለከተ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው “NRERB Research Ethics Review Portal በመጠቀም በኦላይን http://nrerb.ethernet.edu.et ላይ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡