News Detail

National News
Jan 26, 2023 3.6K views

የከፍተኛ ትምህርት ዲጂታል የትምህርት መረጃ ስርዓት ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ

ጥር 16/2015 ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አሰባሰብና አስተዳደርን ለማዘመን የሚረዳ ዲጂታል የትምህርት መረጃ ስርዓት ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
ትምህርት ሚኒስቴር በዲጂታል የትምህርት መረጃ ስርዓት አጠቃቀም ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓትና ኣይሲቲ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ ዲጂታል ስርዓቱ ጥራት፣ተዓማኒነትና ወቅታዊነት ያለው መረጃን ወጥነት ባለው መልኩ ለማሰባሰብ፣ ለማደራጀትና ለመተንተን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዲጂታል ስርዓቱ ከዚህ በፊት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የነበሩትን የመረጃ አሰባሰብ፣አተናተንና አስተዳደር ችግሮችን በላቀ ደረጃ የሚፈታ መሆኑም አቶ ሰብስቤ ተናግረዋል ።
የዲጅታል ስርዓቱ ሁሉንም በሀገሪቱ ያሉ የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን በአንድ ቋት አደራጅቶ ለሚፈለገው አላማ በግብዓትነት ለማዋል የሚያስችልና ለአጠቃቀም ቀላልና ቀልጣፋ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ለሚመለከታቸው የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካላት በአዲሱ ዲጂታል ስርዓቱ አጠቃቀምና አስተዳር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተስጥቶ ወደ ተግባር መገባቱም አመልክተዋል።
በውይይቱም ከሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ አግባብንት ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
Recent News
Follow Us