News Detail

National News
Oct 13, 2022 2.6K views

ዛሬ ጠዋት መስከረም 30/2015 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ በደረሰዉ ጉዳት እናዝናለን፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡ ሁኔታቸዉንም መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ በመሆኑ ወላጆች እንዳይደናገጡ እንጠይቃለን፡፡
ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን እየገለጽን ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ እናሳስባለን፡፡
ሁኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የምናሳዉቃችሁ ይሆናል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር!
Recent News
Follow Us