News Detail

National News
Jan 27, 2022 1.2K views

The organized Autonomy Dream team to achieve AAU institutional independence begin its task. The task force elected Prof. Sebsebe Demesew as its Chairman and Dr. Shibru Temesgen as its Secretary.

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነፃ እና እራሱን የቻለ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ የተደራጀው ግብረ ሀይል ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሥራ አመራር ቦርድ ጋር የግብረ ሃይሉን የሥራ ማስጀመሪያና ትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡
መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተጎናፅፈው መስራት እንዲችሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት መልሶ እንዲደራጅ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡
በውይይቱም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቋማዊ ነጻነት መስጠት ከመንግስትም ከማህበረሰቡም ስምምነት የተደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ይህ የለዉጥ ስራ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃማዊ ነጻነትን ማምጣት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ተቋማዊ ነጻነት የሚሰጥ መሆኑንም ገልፀዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ከፍተኛ ተቋማትም የሚስፋፋ መሆኑም ተገልጿል።
የለውጥ ሃዋሪያት ግብረሃይሉም ፕሮፈሰር ሰብስቤ ደምሰውን ሊቀመንበር እንደዚሁም ዶ/ር ሽብሩ ተመስገንን ፀሃፊ አድርጎ በመምረጥ ሥራውን ጀምሯል፡፡
በዉይይቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስራ አመራር ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና የተመረጡ የለዉጥ ሃዋሪያ አባላቶች ተሳትፈዋል፡፡
Recent News
Follow Us