News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 30, 2020 649 views

በአዲስ አበባ የመምህራን ቀን የምስጋና እና የዕውቅና መርሐግብር ተካሄደ።

"መምህራን በቀውስ ውስጥ ይመራሉ ፤ መጪውንም ይተነብያሉ!" በሚል መሪ ቃል አምስተኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን ቀን የምስጋና እና የዕውቅና መርሐግብር ተካሂዷል።

የምስጋና ፕሮግራሙ ዋና አላማ መምህራን እስከዛሬ ላደረጉት አስተዋፅ ለማመስገን እና ለማበረታት መሆኑ ተገልጿል።

በባለፈው የትምህርት ዘመን ታታሪ እና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ርዕሳነ መምህራን ፣መምህራን እና የትምህርት ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ረጅም አመታት ያገለገሉ መምህራን የዕውቀትና ሜዳልያ ተሸልመዋል ።

በዝግጅቱ ላይ በስነምግባር የታነጸ ፣ሀገሩን የሚወድ እና ለመለወጥ የሚጥር ትውልድ ለማፍራት መምህራን በትጋትና በፅናት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል ።

የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን አስፈላጊውን ትኩረት እንደሚሰጥም ተነግሯል ።

Recent News
Follow Us