News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 28, 2025 18 views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ያነሷቸውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦

👉🏾ትምህርት ላይ ዋናው ሥራ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው።
👉🏾በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ክ43 ሚሊየን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መጽሃፍትን በማሳተም ለተማሪዎች አንድ ለአንድ ማድረስ ተችሏል።
👉🏾ለመምህራን ጥራት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በማዘጋጀት በየደረጃው እየተሰጠ ይገኛል።
👉🏾የትምህርት ቤት መገባ ፕሮግራም ወላጆች ሳይጨነቁ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ በእጅጉ አግዟል።
👉🏾በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብረው አስደናቂ ተግባር እየፈጸሙ ነው።
👉🏾መንግስት እያካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን በማስወገድ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጻኦ አበርክቷል፣
👉🏾ልጆቻችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር አንችልም በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Recent News
Follow Us