News Detail
Oct 27, 2020
632 views
እገዳ የተጣለበት ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመከተል እና ወላጆች ባቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ እገዳ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የግሪክ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እገዳው ተነሳለት፡፡
እገዳው የተነሳው ትምህርት ሚኒስቴር ባቋቋመው ቡድን ባደረገው የሱፐርቪዝን ስራ መሰረት ትምህርት ቤቱ አስፈላጊውን መስተካከያ በማድረጉ እና ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ትምህርት ቤቱም ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራውን ማከናውን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ሌሎች ትመህርት ቤቶችም ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያ በመከተል የመማር ማስተማር ሄደቱን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡