News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 29, 2020 501 views

በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አማካኝነት የተገነባው ትምህርት ቤት።

በቦረና ዞን በዱቡሉቅ ወረዳ የሚገኝ ትምህርት ቤት ነው ፤ ትምህርት ቤቱ ግድግዳው ከእንጨት፣ ጣሪያው ደግሞ በላስቲክ የተሸፈነ፤ የተገነባውም በአካባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎ ነበር።

ጣሪያውም የሚያፈስ ፣ ለተማሪዎች የሚሆን መቀመጫ ያልተሰራለት ስለነበር ተማሪዎች ይቀመጡ የነበረው በዱካ በተገኘው ነገር ላይ ነው።

ባለፈው ዓመት ይህን ትምህርት ቤት የሚያሳይ ምሰል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ምስሉን ተቀባበሉት።

ምስሉ ከተሰራጨ በሃላ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የሚገኙ ሰዎች ትምህርት ቤቱን ለማደስ ባደረጉት እርብርብ በአጭር ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ብር ተሰበሰበ።

አሁን ያ ደሳሳ ጎጆ ትምህርት ቤት በአዲስ ተተክቶ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ለግንባታውም አንድ ሚሊዮን የሚሆን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ገንዘቡም በፌስቡክ በኩል በተደረግው ጥሪ የተሰበሰበ ነው።

አሁን ተማሪዎች ፀሀይ እና ዝናብ ሳይነካቸው የመቀመጫ ወንበር ላይ ሆነው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ። ይህ ሁሉ የሆነው በህብረተሰቡ ተሳትፎ ስለሆነ በዚህ ተግባር ላይ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና ይገባል።

በፌስቡክ እንዲህ አይነት መልካም ስራዎችን፣ የኅብረተሰቡን ችግር የመቀርፍና በቋሚነት የሚያገለግል ስራዎችን መስራት እንደሚቻል ያሳየ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ የለውጥ መሰረት እንደሆነ ያስመሰከረ ተግባር ነው።

ማህበራዊ ሚዲያን ማህበረሰብን የሚጠቅም ነገር ለመስራት፣ ለመማሪያና ለበጎ አድራጎት ስራ እንጠቀምበት! !

Recent News
Follow Us