News Detail
Mar 29, 2025
101 views
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፍልሰት ዙሪያ በሳይንሳዊ ምርምሮች የተደገፉ ስራዎችን በማቅረብ ችግሩ እንዲቀረፍ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።
ትምህርት ሚኒስቴር ዴዚም /Dezim / እና ሶሊሲቲ/ Soli*City/ ከተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡።
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በስደተኝነና ፍልሰት ዙሪያ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በማድረግ ለፖሊሲ ግብኣት የሚሆኑ ሀሳቦችን ሊያመነጩ ይገባል፡።
ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በቅርቡ ከተፈራረማቸው KPI / ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች/ ውስጥ አንዱ ዩኒቨርስቲዎች እንደሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ሕገ-ወጥ ፍልሰትን በመከላከል ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገኝበት ጠቁመዋል፡፡
በተለይም ችግሩ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መንግስት ችግሩን ለመቀነስ የሚያካሂደውን የፖሊሲ እርምጃ ለመደፍና ወደፊት ለማራመድ ጥልቅ ምርምር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
ዴዚል እና ሶሊሲቲ ከተባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ተቋማቱ የተሻለ ምርምር ለመስራት እድል እንደሚፈጥርላቸውም ክቡር ሚኒስተር ዴኤታው አመልክተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሀንዲሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የፍልሰተኝነትና ስደተኝንነት ችግሮች በምርምር ከመፍታት አንጻር ሰፊ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ራሳቸውን በመፈተሽ በምርምር የተደገፉ ተጽዕኖ ፈጣሪ መረጃዎችን ማመንጨት፣ ወደሌሎች ተቋማት ማስፋትና በተጠያቂነትና በኃላፊነት ችግሩን በጋራ ለመፍታት መስራት እንደሚገባቸውም ዶ/ር ሰራዊት ጨምረው ገልጸዋል፡፡፡
ሶሊሲቲን በመወከል የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት ፕሮፌሰር ሃራልድ ባውደር በበኩላቸው ትብብሩ በአፍሪካ ቀንድ በኩል የሚደረገውን ፍልሰት በመረዳት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ለማውጣትና ለችግር የተጋለጡ ስደተኖችንና ፍልሰተኖችን ለመርዳት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡።
የጀርመን የውህደት እና የፍልሰት ጥናት ማእከል (DeZIM) ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኖአ ኬ ሃ በበኩላቸው ስምምነቱ ተቋማቸው በፍልሰተኞችና ስደተኞች ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከዩኒቨርሲቲ የምርምር ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚያስችለው ተናግረዋል፡።
በፊርማ ስምምነቱ ወቅት በፍልሰት ላይ የሚሰሩ የሰባት ዩኒቨርስቲ የምርምር ምክትል ፕሬዚዳንቶች ፣ የፍትህ ሚኒስቴርና ከሌሎችም የተውጣጡ ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።
Recent News
የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ብቃት ማዕቀፍ ለትግበራ መሆኑ ተገለጸ፤
Mar 14, 2025
የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፤
Mar 14, 2025