News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Mar 22, 2025 545 views

ኢትዮጵያ እና ፊላንድ በትምህርቱ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ዙሪያ ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በትምህርቱ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትምህርት ዘርፍ የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ተግባራትን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተውለቸዋል።
በተለይም ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች በሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በዚህም ማናቸውም የሚደረጉ ድጋፎች በመነጋገር ካለምንም የሀብት መባከን በትክክል ህፃናት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል
የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የአካቶ ትምህርት ማዕከላትን በማስፋፋት ረገድ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አሁንም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በምንሰራቸው የለውጥ ተግባራት የበለጠ ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።
በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የላቲን አሜሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ሄሌና አይራክሲነን በበኩላቸው በትምህርቱ ዘርፍ ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በርካታ ተግባራትን ማከናወኗን ጠቅሰዋል።
ይህንን በማጠናከር በትምህርቱ ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ትብብሮችን ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።
ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይት በትምህርቱ ዘርፍ በርካታ ትብብር የሚያደርጉባቸው ጉዳዮች እንዳሉ የተወያዩ ሲሆን ማናቸውም የሚደረጉ ድጋፎች በሚኒስቴሩ በተለዩ የቅድሚያ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ እንዲሆንም ተስማምተዋል።
Recent News
Follow Us