News Detail
Mar 31, 2025
136 views
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በ2017 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ የቁልፍ አፈጻጸም አመላካች ተግባራት እቅድ ላይ ከዘርፉ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ውል ተፈራረሙ፤
የከፍትኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ውሉን የተፈራረሙት መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች የአስተዳደርና መሰረተ ልማት፣የአካዳሚክ ጉዳዮች፣የምርምርና ማህበተሰብ ጉድኝት እና የኣይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ናቸው፡፡
የተፈረመው ውል ሀላፊነትና ተጠያቂነትን በማስፈን የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ጥራት ለማስጠበቅ እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
የመግባቢያ ስምምነት ውል መፈራረሙ ውጤት የሚያስመዘግቡ ሥራ አስፋጻሚዎች የበለጠ የሚበረታቱበት፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚያስመዘግቡት ደግሞ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሥርዓትን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሆነም ተገልጿል።
የመግባቢያ ስምምነቱ ውል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የክትትልና ግምገማ ሥርዓት እንዲኖርና ስራ አስፈጻሚዎች በተልዕኳቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ እንደሚያደርግም ተመላክቷል።
በመሆኑም አራቱም የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚዎች በገቡት የመግባቢያ ስምምነት ውል መሠረት ስራዎቻቸውን ወደ ስራ ክፍሎች (ዴስኮች) በማውረድና ጠንክሮ በመስራት ቀጣይነት ያለው ውጤት ማስመዝገብ አንደሚጠበቅባቸው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
ከወራት በፊት ትምህርት ሚኒስቴር ተመሳሳይ የመግባቢያ ስምምነት ውል ከ47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መፈራረሙ የሚታወስ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል የተፈራረሙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹን በመወከል የተፈራረሙት የየዩኒቨርስቲዎቹ የአስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢዎችና ፕሬዚዳንቶች መሆናቸው ይታወሳል።
Recent News
የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ብቃት ማዕቀፍ ለትግበራ መሆኑ ተገለጸ፤
Mar 14, 2025
የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፤
Mar 14, 2025