News Detail
በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ ያሉ ህፃናትን ለመታደግ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና ትብብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
"Education cannnot wait" በተሰኘ ድርጅት አማካኝነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ)፣ የቦርኪናፋሶና የሶማሊያ ትምህርት ሚኒስትሮች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ወጣቶችና ተፅዕኖ ፋጣሪዎች ተሳትፈዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛና የድርጅቱ ሊቀመንበር ጎርደን ብራወን 4.5 ሚሊየን ህፃናት በግጭትና በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታቸው በመፈናቀላቸው አስቸኳይ ትብብርና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ለህፃናት የምትመች አለምን ለመፍጠርም መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
በዌብናሩ የቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) ኢትዮጵያ በርካታ ስደተኞችን የምታስናግድ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው በስደተኛ ካምፕ ውስጥና በተለያዩ ችግር ውስጥ ያሉ ህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ አጋር አካላት ለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነዋል።
የኮቪድ 19ኝ ተፅዕኖ የተጨመረበትን ይህንን ችግር ለመቅረፍ ትብብርና የፖለቲካ ቁርጥኝነት እንደሚያስፈልግ የዝግጅቱ ተሳታፊዎች አብራርተዋል።
በገንዘብ ማሰባሰቢያና የማንቂያ ዝግጅቱ ላይ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ኔዘርላንድና ኖሮዌይ የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተሰማምተዋል።
ችግር መፍትሄን ይዞ ይመጣል ያሉት የEducation cannnot wait ዳይሬክተር ያስሚን ሸሪፍ የህፃናት የወደፊት እጣ ፈንታን አሁን ማስተካከል አለብን ብለዋል።
በዝግጅቱ ለተሳተፉና ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።