News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Aug 08, 2024 1.2K views

በክረምት የሚሠጠው የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ስልጠና የሙያ ብቃት የሚሻሻልበት መሆኑ ተገለጸ።

በትምህርት ሚኒሰቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ እንደገለጹት ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች በክረምቱ እየተሠጠ ያለው ስልጠና ዓላማ መምህራን በሚያስተምሩበት የትምህርት አይነትና የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ብቃታቸው እንዲሻሻል እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራሮችም መማር ማስተማሩን መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ነው ብለዋል።
ዶር ሙሉቀን አያይዘውም ከትምህርት ሚኒስቴር የሪፎርም ስራዎች አንዱ የመምህራንን የሙያ ብቃት ማሳደግ በመሆኑ የተጀመረው ሥራ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል።
በተጨማሪም ሠልጣኞች በስልጠና ወቅት በሚሠጣቸው ምዘና የሚያገኙት የምሥክር ወረቀት ስልጠናውን በአግባቡ መከታተላቸውን የሚያረጋግጥ ሲሆን በስልጠናው አጥጋቢ ውጤት ያላመጡት በቀጣይ የምዘና ሂደት ውስጥ የሚያልፉበት እድል እንደሚመቻች ገልጸዋል።
በመጨረሻም ስልጠናው በታቀደለት ዓላማ በተቀመጠለት ጊዜ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ ሲሆን በሠልጣኞች በኩል የሚነሱ ችግሮችንም ከክልል ትምህርት ቢሮዎችና ከዩኒቨርስቲዎች ጋር እየተነጋገርን እንዲፈቱ እየተደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
Recent News
Follow Us