News Detail
Aug 09, 2024
1.1K views
በአገር አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የዘንድሮው የክረምት የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግና አልጎሪዚም ሥልጠና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ
በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ ቁልፍ መልዕከት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል ዕወቀት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት አለሙ ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ኮምፒውተር ችሎታ ያላቸው ዜጎችን ማፍራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው መርሃ-ግብሩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ካስተዋወቁት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ፕሮግራም ጋር የሚጣጣም መሆኑን አንስተዋል፡፡
ወ/ሮ ሰላማዊት አክለውም በቀጣይ ጊዜያት የሥልጠናውን ቀጣይነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ ተደራሸነቱና ጥራቱም እንዲጨምር ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ ኮደር ጋር በትብብር የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ ኮደር መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሠር ጂላኒ ኒልሰን በበኩላቸው ሥልጠናው በመስኩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸውን ከ9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎቸን በመመልመል እውቀታቸውንና ከህሎታቸውን በማሳደግ በቀጣይ ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ብቁ ዜጎችን ማፍራት አላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመስኩ ልምድ ያላቸው 26 የአገር ውስጥና የውጪ ሀገራት በጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች እና 99 ተማሪዎች የስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ለ7ኛ ጊዜ የተሰጠውን ስልጠና የትምህርት ሚኒስቴር አዲሰ ኮደር ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024