News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Feb 23, 2024 1.2K views

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን  ዲገሉ ጢጆ ወረዳ ለሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሚኒስትር ደኤታዋ ክብርት ወይዘሮ አየለች እሸቴ  በአርሲ ዞን  ዲገሉ ጢጆ  ወረዳ በሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ለሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀምጠዋል ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ  የኦሮሚያ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ጨምሮ የሠዎች ለሠዎች ድርጅት ተወካይ እና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሀገሪቱን  በአለም ተወዳዳሪ ማድረግ የሚቻለው  በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በግብረገብ የታነፁ ተማሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን አንስተው ለዚህም ጠንክሮ መስራት ይባል ነው ያሉት፡፡

አክለውም የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የሚቻለው በትምህርት ቤት ምቹ የትምህርት ከባቢን መፍጠር ሲቻል መሆኑን ያነሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ለዚህም ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የሠዎች ለሠዎች ግብረ ሰናይ ድርጅትም ትምህርት ቤቱን ለመገንባት ላደረገው ድገፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ  ትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ስብራትን ለመጠገን ከሚያደረገው ጥረቶች አንዱ የሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ እንዲጀመር የትምህርት ሚኒስቴርና ሰዎች ለሰዎች  ላደረገው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ግንባታ እስኪጠናቀቅም ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ግንባታውን የሚያከናውነው የሠዎች ለሠዎች ድርጅት ተወካይ አቶ ይልማ በበኩላቸው ድርጅቱ የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሠራ ሲሆን 20 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር መግባባቱን አንስተው ዛሬ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠው አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

የግንባታው አጠቃላይ ወጪ ሰዎች ለሰዎች ግብረ-ሠናይ ድርጅት  የሚሸፈን ሲሆን እስከ መስከረም  ይጠናቀቃልም ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና ለመቀየር ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንዳለ ይታወቃል።

Recent News
Follow Us