News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Feb 29, 2024 1.5K views

የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን የካቲት 22/2016 ዓ.ም ይከበራል!

የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ነገ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ይከበራል።
የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እኤአ አቆጣጠር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲከበር በወሰኑት መሠረት የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በየአመቱ ማርች አንድ በህብረቱ አባል ሀገራት አስተናጋጅነት እየተከበረ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡
 
በዚህ አመትም 9ኛው የአፍሪካ ትምህርት ቤት ምገባ ቀን "አካታችና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ላይ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይገባል” በሚል መሪ ቃል ነገ በድሬደዋ ከተማ ይከበራል፡፡
 
በኢትዮጵያ ከ6.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሲሆኑ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ማጠናከር መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ የሁሉንም ዜጋ ትብብር ይሻል!
Recent News
Follow Us