News Detail
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ የትምህርት ዘርፍ ረዳት ዳይሬክተር ጀኔራል ጋር ውይይት አካሄዱ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ የዩኔስኮ የትምህርት ዘርፍ ረዳት ዳይሬክተር ጀኔራል ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱ የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመደገፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የትምህርት ስርአቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመደገፍና ለማዘመን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አስመልክቶ ክቡር ሚኒስትሩ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ኦንላይን እየተሰጠ መሆኑን በአብነት አንስተዋል፡፡
በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ከኩረጃና ስርቆት ለመከላከል በኦንላይን ለመስጠት እና ሁሉንም አይነት የትምህርት መረጃዎች ወደ ዲጂታል የመለወጥ ጅምር ስራዎች ያሉ መሆኑን በመግለጽ ዩኔስኮ ግብአቶችን በማሟላት ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል፡፡
በዩኔስኮ የትምህርት ዘርፍ ረዳት ዳይሬክተር ጀኔራል ስቴፋኒያ ጃኒኒ በበኩላቸው ዩኔስኮ ሀገሪቱ የትምህርት ዘርፉን በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እየደገፈ ሲሆን በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024