News Detail
Feb 20, 2024
1.2K views
የፊንላንድ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የሁለቱ ወገኖች ውይይት ያተኮረው በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን በዋነኝነትም በአካቶ እና የልዩ ፍለጎት ትምህርት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በውይይቱ ወቅት ባደረጉት ገለጻ ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት ውስጥ የፊንላንድ መንግሰትና ህዝብ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ እያይዘው በኢትዮጵያና ፊንላንድ መንግሰት መካከል ያለው ዘላቂ የትምህርት ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ትብብር ማሳያ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ፡፡
በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ክብርት አምባሳደሯ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ገለጻ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በትምህርቱ ዘርፍ በተለይም በአካቶና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024