News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 13, 2022 3.1K views

የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ተጠናቋል

የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመጀመሪያው ዙር ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ133 ማዕከላት ተፈትነዋል።
ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በደረሰው ክስተትም የመጀመሪያው ቀን ተፈታኞች ያልተፈተኑ መሆኑንና ያልተፈተኗቸውን ፈተናዎች በቀጣይ ዙር እንደሚፈተኑ ነገር ግን በአንድ አንድ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናውን ጥለው የወጡ ተማሪዎች ከፈተና ውጪ መሆናቸውንና ዳግም የማይፈተኑ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ሚኒስቴሩ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉ አካላትም ምስጋናውን አቅርቧል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
Recent News
Follow Us