News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 01, 2022 2.6K views

የትምህርት ማስረጃዎችን በዲጅታል መያዝ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ተቋማትን መረጀ ማስቀመጥና ማሥተዳደር የሚያስችል "ኢ-ስኩል" የተሰኘ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆኗል።

ቴክኖሎጂው ዋልያ ቴክኖሎጂ በተባለ የግል ድርጅት የበለፀገ ሲሆን የመምህራንና የተማሪዎችን መረጃዎች መያዝ ከማስቻልም ባለፈ  የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያዘምን መሆኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት  ዘርፍ  ሚኒስትር  ዴኤታ   ፋንታ ማንደፍሮ(ዶ/ር) የትምህርት ተቋማት  የመረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን በዲጂታል ቴክኖሎጂ  በመታገዝ ማስቀመጥና ማስተደደር እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ  ምክኒያት በትምህርት ማስረጃዎች ላይ የሚደርሰውን ጥፉት ይቀርፋልም ብለዋል።

ዶ/ር ፋንታ በቅርቡ በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት ከትምህርት ተቋማቱ ባሻገር የትምህርት ማስረጃዎች መውደማቸውን ገልፀው 
ከዚህም ትምህርት በመውሰድ በቀጣይ ትምህርት ቤቶች የመረጃና ማስረጃ አያያዝ ሥርዓታቸውን በማዘመን የመረጃ ማዕከላቸውን በድጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲያስተዳድሩ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዋልያ ቴክኖሎጂ መስራች የሆኑት አቶ አንተነህ አሥራት ዲጂታል ቴክኖሎጂው ትምህርት ቤቶች መረጃና ማስረጃዎችን ዲጂታላይዝ አድርገው እንዲያስቀምጡትና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መጽሃፍትን የሚያገኙበትንም ቤተመጽሃፍትንም ማካተቱ ተገልጿል።

ቴክኖሎጂውን በመጠቀምም የትምህርት ቤት ክፍያዎችን በኦንላይን እንዲከፍሉ የሚያስችል እና ዘረፋ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑም ተጠቅሷል ፡፡

Recent News
Follow Us