News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 06, 2021 1.1K views

መምህራንና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆነው መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ ስራዎች ህዝባቸውን እንዲያግዙ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ ይሰማራሉ።
ሰብል መሰብስብ፣ በግንባር ላሉ ለኢትዮጵያ ኃይሎች ድጋፍ ማሰባሰብ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እና ደም መለገስ የዘመቻው አካል ነው።
ተማሪዎችና መምህራን አቅማቸው በሚፈቀድውና በሚችሉት መልኩ ህዝባቸውን ለአንድ ሳምንት ያገለግላሉ።
የበጎ ፍቃድ የዘመቻ ስራው በሁሉም ክልሎች የሚደረግ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች ይሳተፋሉ።
Recent News
Follow Us