News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 02, 2021 1.1K views

ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል የቀሰሙትን እውቀት ወደ ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤት ለመቀየር በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተገለፀ

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞለ6ኛ ጊዜ የዓለም አቀፍ የሣይንስ ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡ በመርሀ ግብር ላይ በአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን የተሰሩ በርካታ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል፡፡

የሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል  ሰለሞን ቢኖር (ዶ/ር)  ውድድሩ የሣይንስ ዘርፍ ለማህበረሰብና አገር እድገት ያለውን ሚና ለማሳወቅ አስፈላጊ  መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ 

ውድድሩ አገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር ልምምድ ከማዳበርም ባሻገር በሳይንሲና ቴክኖሎጂ  የፈጠራ ሥራ ባለቤት ሆነው ወደፊት በሚፈልጉትና በሚችሉት ሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩ በር ይከፍታልም ብለዋል ፡፡ 

በመድረኩ የሣይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ዳይሬክተር ጄነራል አብርሃም ዓለማየሁ (ዶ/ር) ውድድሩ ከ7ተኛ ክፍል ጀምሮ የአጠዋላይ ትምህርት ተማሪዎች፣ መምህራንና ከተለያዩ ስቴም  (STEM) ማዕከላት የተውጣጡትን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ ተማሪዎች በክፍል የቀሰሙትን የንደፈ ሃሳብ እውቀት ወደ ችግር ፈቺና ጠቃሚ  የፈጠራ ውጤት ለመቀየር መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የስቴም ሲነርጂ ካንትሪ ዳይሬክቴር ወ/ሮ አሰገደች ሻወል በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራውን የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመደገፍ 22 ስቴም በማዕከላትን ያቋቋመ ሲሆን ተማሪዎች በክፍል የተማሩትን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ልምምድ እንዲያዳብሩ  በሥሩ 71 ቤተ ሙከራዎች  መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡ 

በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት በመስጠት በትምህርት አቀባበላቸው ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ለወጡ ተማሪዎች እና ሴት ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ  በማዕከላቱ እንደሚቀላቀሉ አስረድተዋል፡፡
 
በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ከትምህርት ሚኒሰቴር፣ ከስቴም ሲነርጂና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ይዘው የቀረቡ ተማሪዎችና መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

የፈጠራ ሥራ ውድድር መርሃ ግብሩ ለቀጣይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተሻለ ውጤት በማምጣት ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ይበረከታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Recent News
Follow Us