News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 01, 2021 1.1K views

የቀድሞ ትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለግሱ።

የትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት የበጎ ፈቃደኛ ዘማቾች ሽኝት፣ የደም ልገሳ እና የስንቅ ዝግጅት ስራ እያደረገ ባለበት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ነው ደም የለገሱት።
የደም ልገሳ በግንባር ህይወቱን እየሰጠ ለሚዋደቀው የመከላከያ ሰራዊታችን ማድረግ ከምንችለው ትንሹ ነገር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን በሚል በተደጋጋሚ ደም ሲለግሱ የቆዩት ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) "በማንኛውም ጊዜ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅብንን እንወጣለን" ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው እለት ለ32 በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሽኝት ይታወሳል።
Recent News
Follow Us