News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 06, 2021 547 views

ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ትምህርት ቤቶች በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ያሉበትን ደረጃ ይበልጥ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ይህ የተገለጸው ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓመታዊ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አፈጻፀም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡
የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስፋው መኮንን በ2013 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማሻሻል ከተለያዩ የትምህርት ሚኒስቴር ሥራ ክፍሎች እና የክልል እንዲሁም የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በጋር በመቀናጀት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ።
እንደ ዳሬክተሩ ገለፃ ከተከናወኑ በርካታ ሥራዎች መካከል ለአብነት የክትትልና ድጋፍ፣ የአቅም ግንባታ፣ የናሙና ኢንስፔክሽን፣ ድንገተኛ ቅኝት የማድረግ፣ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች ደግም ኢንስፔክሽን የማድረግ ሥራዎችና ለትምህርት ተቋማት የግብር መልስ የመስጠት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል ።
በቀረበው ሪፖርት በበጀት ዓመቱ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ትምህርት ቤቶች በወቅቱ ባለመከፈታቸው የተነሳ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በሚፈለገው ለማሻሻል የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ የማዘጋጀት ውስነቶች መኖራቸውን፣ የበጀት እና የግብዓት አቀርቦት እንደ እጥረት መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
መድረኩ በእቅድ አፈፃፀም ሂደት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ለቀጣይ ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች የተዳሰሱበት ነው።
በውይይቱ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
Recent News
Follow Us