News Detail
Oct 06, 2021
577 views
ትምህርት ሚኒስቴር ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም ትምህርት ነክ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ ር ኢንጅ) የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት በትምህርት ቤቶች የሚስተዋለውን የውሃና ንጽህና አጠባበቅ ችግሮች ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ስምምነቱም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀናጀ መንገድ ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር እንደሚያስችልም ገልፀዋል፡፡
የሮተሪ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ተሾመ ከበደ በበኩላቸው በትምህርት ቤቶች የውሃ አቅርቦቶች እንዲኖር የሚያሰችል ፕሮጀክት መዘጋጀቱን ገልፀው በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቶች እያደረጉ እንዳለም ገልፀዋል፡፡
ሮተሪ ኢንተርናሽናል የተለያዩ ስራዎችን በትምህርት ዘርፉ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024