News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jun 16, 2021 746 views

የብሔራዊ ዩኔስኮ ጽህፈት ቤት ስራዎችንና ግንኙነትን የሚያሳልጥ አዲስ አሰራር ይዘረጋል ተባለ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ቴክኒካል እና ስትሪንግ ኮሚቴ የስራ አፈፃፀሙ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
ውይይቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤት ስትሪንግና ቴክኒካል ኮሚቴ አባላትና ተወካዮች በተገኙበት በትምህርት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት ነው የትካሄደው።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤት እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤት ያለፈውን በማረም የወደፊቱን በማለም ትክክለኛ ስራ እንዲሰራ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ የትምህርት ሚኒስቴር ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤቱን መልሶ በማደራጀት አቅም ባላቸው ባለሙያዎች የማደራጀት ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤቱ በሁሉም አባል መስሪያ ቤቶች የተሰሩ ስራዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ለመጫን እንዲሁም በፓሪስ ከሚገኘው የዩኔስኮ ዋና ጽ/ቤት ጋር ለመገናኘት የሚያስችል አዲስ ፕላትፎርም/ National UNESCO dash board software /በአጭር ጊዜ ይዘረጋል ብለዋል።
በፓሪስ የኢፌዴሪ ሚሲዮን በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የስራ ደረጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ምክትል ቋሚ መልእክተኛ የሆኑት ጥላዬ ጌቴ (ፒ ኤች ዲ) በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤት ሰብሳቢነት በአዋጅ የተሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር አደረጃጀቱን ማጠናከር ይገባዋል ብለዋል።
በብሔራዊ ዩኔስኮ ጽ/ቤቱ እስካሁን በጋራ የመስራት ስራው ባለመሰራቱ ምክንያት የተሰራው ስራ የተበታተነ እንዲሁም ሚዛን የሚደፋ አለመሆኑን ጠቅሰው ይህንን ከመሰረቱ መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች የተሳታፉ ሲሆን ጽ/ቤቱን ለማጠናከር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ተደርጓል፡፡
Recent News
Follow Us