News Detail
        
            Jan 26, 2021
        
        
            
            661 views
        
    
    
    
    ሀገር አቀፍ የ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ›› ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች ሊጀመር ነው፡፡
                    የትምህርት ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሀገር አቀፍ የ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ›› ንቅናቄ ማስጀመሪያን የተመለከተ ማብራሪ ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡ 
                    
                
            የትምህር ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሰሞን የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው መልኩ ሲተገበሩ ቢቆዩም በቅርቡ ግን መዘናጋቶች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡
ይህ መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍል ‹‹የእንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ›› ንቅናቄ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከጥር 25 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የወረርሽኙ ስርጭት በመጨመሩና በፍጥነት የሚዛመት አዲስ የኮሮና ተዋህሲ በመገኘቱ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ወረርሽኙ ተባብሶ ዳግም ትምህር ቤቶች እንዳይዘጉና ዋጋ እንዳያስከፍልን ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡
ንቅናቄው ጥር 25 የሚጀመር ሲሆን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያሉ ተመሪዎች መምህራንና የትምህርት ሰራተኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አቅራቢያ በእግር በመጓዝ ‹‹እንድናገለግል ማስክ ያድርጉ›› የሚል ግንዛቤ ይሰጣሉ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ90 በመቶ በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸውን ጀምረዋል፡፡