News Detail
        
            Jan 26, 2021
        
        
            
            558 views
        
    
    
    
    የቻይና የንግድ ምክር ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
                    ድጋፉ ዳግም በተከፈቱ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የተደረገ ነው። 
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ከቻይና ኢምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሊዩ ዩና የካምፓኒ ተወካዮች ቁሳቁሶቹን ተረክበዋል። 
                    
                
            ድጋፉ 500ሺ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልና 11ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ናቸው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ድጋፉ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል የተጀመረውን የመማር ማስተማር ስራ በማገዝ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቁ ያግዛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በምታደረገው ጥረት ውስጥ የቻይና መንግስትና የንግድ ማህበረሰብ ድጋፍ ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የቻይና የንግድ ምክር ቤት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የቻይና ኢምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሊዩ ዩ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ የቻይና መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና የንግድ ምክር ቤት አምቡላንሶችንና አጋዥ የመተንፈቫ መሳሪያዎችን ጨምሮ በሀገር ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች እንዲመረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።