News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jan 27, 2021 746 views

500 ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮጀክት ይፉ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከህፃናት አድን ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ሰፉ ያለ አካታች ሀገር በቀል የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
በምገባ ፕሮግራሙም ወደ 500 ትምህርት ቤቶች የሚታቀፉ ሲሆን በዚህም ከ 163ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባው አካል እንደሚሆኑ ተነግሯል።
 
ፕሮግራሙ በ 5 ክልሎች ውስጥ ባሉ 13 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።
 
በፕርግራሙም ቅድመ መደበኛ እና አንደኛደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካተቱ ሲሆን ለ አንድ አመት እንደሚቆይም ተነግሯል።
 
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚለዬን ማቲዎስ ፕሮጀክቱ የነገ ተስፋ የሆኑ ህፃናት ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ እና በትምህርት ቤት ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ ትልቅ አስተዋጾ አለው ብለዋል።
የህፃናት አድን ድርጅት በኢትዬጵያ ዋና ዳይሬክተር ኢኪን ኦጉቶጉላሪ በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ድርጅቱ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል አንዱ በመሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
 
የምገባ ፕሮግራሙ በተፈጥሮ እና በአንዳንድ ምክንያቶች የተጎዱ እና ከዚህ በፊት ድጋፍ ያልተደረገላቸው አካባቢዎችን የሚያካትት መሆኑም ተገልጿል።
 
ፕሮጀክቱ ይፋ የሆነው Global partnership for education በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አማካኝነት ነው።
 
ከዚህ ቀደም ሀገር በቀል የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳ
Recent News
Follow Us