News Detail
Jan 29, 2021
621 views
የትምህርት ሚኒስቴር ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር እና ዲቦራ ፋውንዴሽን በትምህርት ዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በመግባቢያ ሰነድ ፊርማው ላይም የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ስምምነቱ አካታች ሁሉን አቀፍ እና ፍትሃዊ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እና ዘላቂ የትምህርት እድል ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ ዓላማ የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ሕፃናትን ለማስተማር የሚያስችል የመምህራን የሥልጠና መርሃ ግብር እንዲኖር ለማድረግ እና ሁሉን አቀፍ ጥራት ያለው ትምህርት አቅርቦት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ያለመ መሆኑም በስምምነቱ ተገልጿል፡፡
ለመንግስት ትምህርት ቤቶች እና ለመምህራን የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሃግብሮችን በማዘጋጀት የአዕምሮ ችግር ላለባቸው ልጆች ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ሥልጠናና ትምህርት ለመስጠት መታሰቡንም በስምምነቱ ተነስቷል፡፡
ስምምነቱም የአዕምሮ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች አቅርቦት እና ስርጭት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ እና የአዕምሮ ችግር ላለባቸው ልጆች የትምህርት መብትን ለመደገፍ እንደሚያስችል ተጠቅሷል፡፡