News Detail

National News
Dec 27, 2025 20 views

የዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመጥን አሰራርና አደረጃጀት እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤

የጅማ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ጌንት የ25 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎለታል።
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመጥናቸው አሰራርና አደረጃጀት እንዲኖር እየተሰራ ይገኛል።
‎የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች እንደሀገር እሰከ 80 በመቶ የሚደርስ የክሊኒካል አገልግሎት ጫና እንዳለባቸው የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታትም አየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
‎የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ለዩኒቨርስቲው ህክምና ማዕከል የተደረገው የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ሆስፒታሉ የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችለው ጠቅሰዋል።
‎ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የጅማ ዩኒቨርስቲን ልዩ ልዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
Recent News
Follow Us