News Detail

National News
Apr 14, 2025 20 views

የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ብቃት በማሻሻል ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ለማድረስ እተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ሁሉ ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል።
በሁሉም መስክ ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው መሀንዲሶች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ ቴክኒሻኖች፣ ቢሮክራቶችና ሌሎችምም ባለሙያዎች በጥራትና በብቃት ማፍራት ሲቻል መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ፣ የመምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎችም የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።
በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው በትምህርት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት እጅግ ትልቁ ተግባር መሆኑን ጠቁመው ከዚህ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ትምህርት ላይ እየተደረገ ያለው ሪፎርም ሌሎችንም ተቋማት ሊቀይር የሚችል መሆኑን ገልጸው ከቀረበው ሪፖርት ብዙ አበረታች ለውጦች መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደትምህርት ቤት እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር 9 ወራት እቅድ አፈጻጸምና ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡።
Recent News
Follow Us