News Detail

National News
Feb 19, 2025 87 views

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የአርጀቲና አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የአርጀንቲና አምባሳደር ኢግናሲዮ ሮካታግሊታ ጋር በትምህርት ዘርፉ በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል ።
በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ሁለቱ ሀገራት በሚኖራቸው የጋራ ትብብር በትምህርቱ ዘርፍ ሊሰሩባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን አንስተው አብራርተውላቸዋል።
በተለይም በቋንቋ ልማት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን ልውውጥና ነጻ የትምህርት እድል፣ በኪነ ጥበብ፣ ስፖርትና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ለአምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል።
በዚህ ረገድ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር መስራት የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ መኖሩንም ጨምረው አብራርተውላቸዋል።
በኢትዮጵያ የአርጀንቲና አምባሳደር ኢግናሲዮ ሮካታግሊታ በበኩላቸው አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በማሳደግ በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
አክለውም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን ልውውጥና ነጻ የትምህርት እድል፣ በአዳዲስ ፈጠራዎች፣ በኪነ ጥበብ፣ ስፖርት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
Recent News
Follow Us