News Detail
Dec 09, 2024
79 views
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ የጤና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ማድረስ እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተ ክርስቶስ ታምሩ በኤች አይ ቪ እና በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭት እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም በቫይረሱ አዲስ የሚያዙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎች አሉ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎችም የኤች አይ ቪና ስነተዋልዶ ጤና ችግሮች ተጋላጭ በመሆናቸው ከቫይረሱ ነጻ የሆነ ትውልድ እንዲፈጠር በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድም ሰው በኤች አይ ቪ ቫይረስ እንዳይያዝ ሳይዘናጉ መስራትና በሽታውን ለመከላከል የተጀመረውን ጥረት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ተናግረዋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የስነ ተዋልዶ ፣ ቤተሰብ እቅድ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና ዴስክ ተወካዮ አቶ ሞቱማ በቀለ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤች አይ ቪ ብቻ ሳይሆን የስነ ተዋልዶ ጤና ሙሉ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኤች አይ ቪ እና በስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ዙሪያ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ዩኒቨርስቲዎች በስነ ተዋልዶ ችግሮችን በሚመለከት ቢያንስ የ20 እና የ30 ደቂቃ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን አመቻችተው ትምህርት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙ አጋር ተቋማት በበኩላቸው የኤች አይቪ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ሁሉንም የሚያጠቁ የጤና ስጋቶች በመሆናቸው በቅንጅትና በጋራ መቋቋምና መከላከል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ስልጠና በሚገባ ላጠናቀቁ ከዩኒቨርስቲዎች ለተወከሉ ባለድርሻዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024