News Detail
Nov 30, 2024
238 views
2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻልና ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ።
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ትምህርትና በተማሪዎች ቅበላ ዙሪያ ከክልልና ከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርጓል።
በበይነ መረብ ውይይቱ የማጠናከሪያ ትምህርትን እንዲሁም ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን በሚመለከት የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ውጤትን ለመሻሻል የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካለት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ክብርት ወ/ሮ አየለች አክለውም መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና ወላጆች ተማሪዎችን በስነልቦና ዝግጁ የማድረግ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ከተማሪዎች ቅበላ አኳያም ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመው በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣና ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቁ በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በበይነ መረብ ውይይቱ የተሳተፉ የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የ2ኛ ደረጃ የማጠናከሪያ ትምህርት ዕቅድ አውጥቶ ወጥ በሆነ ሁኔታ መሥራት ተገቢ እንደሆነ ገልጸው የታሰበውን ውጤት ለማምጣት ርብርብ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
የትምህርት ቢሮዎቹ አመራሮች በመጨረሻም ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024