News Detail

National News
Aug 23, 2024 711 views

የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ ወረዳ ዋሬርሶ ማሌማ ቀበሌ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አሻራቸውን ያኖሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አረንጓዴ አሻራችንን በማኖር አርአያነታችንንና ቁርጠኝነታችንን ለትውልድ በተግባር ማሳየት ይገባናል ብለዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒሰትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በጉጉት ስንጠብቀው ለነበረው ለዚህ ቀን ደርሰው አረንጓዴ አሻራቸውን በማስቀመጣቸው ደስ ያላቸው መሆኑን ገልጸው ሀገራችን ለዓለም አስተዋጽኦ ያደረገችበት መርሃ-ግብር መሆኑን ተናግረዋል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ችግኞቹን የተከሉት በተራቆተ ቦታ በመሆኑ ከአቻ መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበርም የመንከባከብ ስራ እንደሚሰራ እና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የግድ መሆኑን ተናግረዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው በሁለንተናዊ መልኩ የበለጸገች አገር ለትውልድ ለማውረስ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ኃላፊነታችንን ልንወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሱሉልታ አካባቢ በተካሄደው አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ ግብር የትምህርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
Recent News
Follow Us