News Detail

National News
Feb 21, 2024 977 views

የማላዊ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ::

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሸኔ የማላዊ ትምህርት ሚኒስቴር ሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዳይሬክትር የሆኑትን ፕ/ር ቻሞራ ሜኬካን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ የትብብር መስኮች በተለይም በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ትብብር ለመፍጠር በሚያስችል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡
በተያያዘም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በኩል በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎረም ተግባራትን አስመልክቶ በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በኩል ገለጻ ተደርጓላቸዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የምርምር እና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር ፍላጎት ለመለየት እና ወደፊት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማስጀመር መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Recent News
Follow Us