News Detail

National News
Mar 28, 2023 5.4K views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የመንግስትን የስድስት ወራት ሪፖርት መነሻ በማድረግ በምክር ቤቱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ይገኛል

ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ የተነሱ ጥያቄዎች:-
1)መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት የሰራቸው ስራዎች አበረታች ቢሆኑም አሁንም የተለያዪ ማነቆዎች ይስተዋላሉ
ከነዚህም መካከል የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ መፅሐፍ ማሳተም የፌድራል ድርሻ ቢሆንም እስካሁን ያለመድረሱ፣
የመሠረተ ልማት አቅርቦት የመብራትና ኢንተርኔት ያለመኖር እንዲሁም የመምህራን አቅም ግንባታ እጥረት ለትምህርት ጥራት ችግር ሆነዋል።
የወልዲያ ዩኒቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት ተጎድቶ ለትምህርት ስራ ምቹ ያለመሆኑ ይጠቀሳል።
በመሆኑም በትምህርት ዘርፉ ያለውን ችግር ለማሳካት መንግስት ምን አስቧል የሚል ጥያቄ የተጠየቀ ሲሆን፦
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በምላሻቸው ባለፉት 4 ዓመታት በፍኖተ ካርታው በተቀመጠው መሠረት ዩኒቨርሲቲ አናስፋፋም። ታች ጥራት እናስፋፋለን፣ ፈተናን አውቶሜት አናደርጋለን በሚል ባለፋት ሶስት አራት አመታት ሰፋፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።ኬጂን ማስፋት፣አንደኛ ደረጃ ማስፋት፣ ሁለተኛ ደረጃ ማስፋት፣በተቻለ መጠን የትምህርት ቤት ምገባን ማስፋት ሙከራዎች እየተደረጉ ነው። አሁንም የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ብዙ ስራ የሚጠይቅ ስለሆነ በመጻሀፍትም፣ በኢንተርኔትም በተሻሉ መምህራን ገና ሰፋፊ ስራዎች ይጠበቁብናል። ጅማሮዎቹ የሚታወቁ ናቸው እነዛን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል።
Recent News
Follow Us