News Detail

National News
Jan 24, 2023 3.7K views

አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በትምህርቱ ዘርፍ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ተገለፀ

ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ከምሁራን ጋር ምክክር እያካሄደ ነው ።

ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ከምሁራን ጋር ምክክር እያካሄደ ነው ።

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ረቂቅ ፖሊሲው በተለያዩ ጊዜያት ምክክር ሲደረግበት የቆየ መሆኑን እና በትምህርቱ ዘርፍ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው የታሰቡ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል።

በትምህርት ሥርዓቱ የደረሰውን ስብራት ለማከም ፖሊሲ መቅረፅ ብቻውን ለውጥ አያመጣም ያሉት ሚኒስትሩ ያሉ ስብራቶችን በሙሉ ለመቅረፍ በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።

ፓሊሲው በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው የቀረቡ ምክረ ሀሳቦችን በመመልከት በትምህርቱ ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን ሊፈታ በሚችልና አለም አቀፍ ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ መዘጋጀቱም ተገልጿል።

በቀጣይም የፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች፣ የህግ ማዕቀፎች እና ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁም ነው የተነገረው።

ፓሊሲውን ለመተግበርም የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅም በመድረኩ ተነስቷል።

የረቂቅ ፖሊሲው ዋና ዋና ሀሳቦች የትምህርት ሚኒስትር የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ በሆኑት ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) ቀርቦ ውይይትም ተደርጎበታል።

በምክክር መድረኩ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣ ከስራና ክህሎትና ሌሎች ሚኒስቴር መ/ቤቶች፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ከመምህራን ማህበር፣ ከትምህርት አማካሪ ምክር ቤት፣ የተለያዩ የሞያ ማህበራትና ሌሎች አጋር ተቋማት የተውጣጡ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

Recent News
Follow Us