News Detail

National News
Nov 30, 2022 3.5K views

በትግበራ ላይ ላለው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ውጤታማነት የሁሉም ባለድርሻዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ።

ህዳር 12/2015ዓም.(ትምህርት ሚኒስቴር) ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል፡ከተማ አስተዳደሮችና ከተመረጡ የሀገሪቷ የመምህራን ኮሌጆች ለተውጣጡ ባለሙያዎችና መምህራን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ስኬታማነት ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን ያስጀመሩት የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ተወካይ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ በትግበራ ላይ ላለው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ውጤታማነት የሁሉም ባለድርሻዎች ተሳትፎ ወሳኝ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስርዓተ ትምህርቱ አገራዊ ፣ ሙያዊና አሳታፊ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ ተሳታፊዎቹ ተቀናጅተው ለስርዓተ ትምህርቱ ስኬታማነት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በየደረጃው ለሚገኙ የስርዓተ ትምህርቱ አስፈፃሚዎች በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠት ማብቃት እንዳለባቸውም ወ/ሮ ዛፉ አስገንዝበዋል።
የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ አቶ ኡመር ኢማም በበኩላቸው የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት በሁለንተናዊ መልኩ መተግበር ለቀጣይ የትምህርት ደረጃዎች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋዋጽኦ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ኡመር አክለውም አዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ከስነ-ምግባር፥ከክህሎትና ከእውቀት አንጻር ሀገራችን የምትፈልጋቸውን ንቁና ብቁ ዜጎች ለማፍራት ለሚሰሩ ዘለቄታዊ ስራዎች መሰረት ለመጣል የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
Recent News
Follow Us