News Detail

National News
Nov 09, 2022 3K views

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መስጫ ማዕከላትን ጎበኙ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መስጫ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ተማሪዎችን አግኝተው በርትተው እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
አክለውም አሁን የደረሱበት ደረጃ የደረሱት ከመሠረተ ትምህርት ተነስተው መሆኑን በመግለጽ የህይወት ተሞክሯቸውን ለጎልማሶቹ አካፍለዋል።
ማንበብ፣ መፃፍና ማስላት ለመቻል የተሻለ ህይወትን ለመምራት ሌሎችም እንዲመጡና እንዲማሩ አድርጉ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገር መለወጥ የምትችለው ትምህርት ላይ በሚሠራ ስራ ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው በሁሉም አማራጮች ዜጎች ትምህርት እንዲያገኙ መስራት ይገባልም ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮሴፍ አበራ በበኩላቸው የጎልማሶች ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ በጉብኝቱ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር 113 የሚደርሱ መደበኛ ትምህርት ቤትን መሠረት ያደረጉ የጎልማሳ ትምህርት መስጫ ማዕከላት መኖራቸው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
Recent News
Follow Us