News Detail

National News
Oct 26, 2022 3.4K views

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደሆነ ተገለፀ፡፡

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደነበር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአግባቡ ከተመሩ፣ ከቆረጡና ጥረት ካደረጉ የትኛውንም ተልዕኮ መወጣት እንደሚችሉ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም መላው ህዝባችንም ሲያማርርባቸው የነበሩ ጉዳዮችን መንግስት ለማረም ሲነሳና ጥረት ሲያደርግ ድጋፍ እንደሚሰጡ በተጨባጭ የተረጋገጠበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
አክለውም በቀጣይ እንደ ሀገር ህዝቡ በሚያማርርባቸው የተደራጀ ሌብነት፣መልካም አስተዳደር እጦት፣ለመንግስት አገልግሎት እጅ መንሻ መጠየቅ ላይ እንዲሁም በትምህርት ሴክተሩ ሃሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለማስተካከል ህዝቡን ከጎናችን ካሰለፍን ትርጉም ባለው መልኩ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ትምህርት ተወስዶበታል ብለዋል፡፡
የፈተና አስፈፃሚዎች ከተወለዱበትና ከሚያስተምሩበት ውጪ መመደባቸው ኢትዮጵያውያን አሁንም የተሳሰርንበትና የተጋመድንበት ጠንካራ ማህበራዊ ትስርስር ያለን መሆኑን የተረዳንበት ነበርም ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ፡፡
አጠቃላይ ሂደቱ የሚኒስቴር መስሪያቤቱን ቅቡልነት መልሶ ለመገንባት እድል የተፈጠረበት መሆኑን ጠቅሰው በትምህርት ሴክተሩ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ መተግባርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አፈፃፀም ዙሪያ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
Recent News
Follow Us