News Detail

National News
May 14, 2021 315 views

የትምህርት ሚኒስቴር ራሳ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በህንድ ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ) እና የራሳ ማኔጅመንት እና የማማከር ድርጅት ስራ አስኪያጅ ራጃሽ ሞሲስ (ፒ ኤች ዲ) ፈርመውታል።

የነፃ የትምህርት እድሉ ከአጫጭር ስልጠና እስከ ፒ ኤች ዲ የሚደርሱ ፕሮግራሞችን የያዘ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንን አቅም ለማሳደግ በሚያደገው ጥረት ውስጥ እንዲህ ያሉ የነፃ የትምህርት እድሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። 

ኩባንያው ከዚህ በፊት ከ1ሺ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በህንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች እና መስኮች ነፃ የትምህርት እድል ሲሰጥ ቆይታል። 

በቀጣይ ከ5ሺ በላይ ከሚሆኑ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ የራሳ ማኔጅመንት ስራ አስኪያ ራጃ ሞሲስ (ፒ ኤች ዲ) ጠቁመዋል። 

ነፃ የትምህርት እድሎቹ ህንድ በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ አጫጭር ስልጠና፣ የዲግሪ፣ የማስተርስ እና የፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞችን ያካተተ ነው።

Recent News
Follow Us