News Detail

National News
May 21, 2026 53 views

በትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የ5 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት ተፈረመ፤

በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዩናይትድ ኪንግደም የውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሻሻል የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በለንደን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የአለም የትምህርት ፎረም 2026 ጎን ለጎን የትምህርት ሚኒስቴር፣ በውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮ (FCDO) እና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከርና ለማሻሻል የሚያስችል የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራን አቅምን ለማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ተገልጿል።
ይህ ስምምነት የአምስት ሚሊየን ፓውንድ ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ተብሏል።
በተጨማሪም ስምምነቱ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ዓለም አቀፍ ትብብር የሚያጠናክር ሲሆን፣ ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የቋንቋ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
Recent News
Follow Us