News Detail

National News
Mar 23, 2026 33 views

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተዘጋጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ፣ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ ደንብ ፣ ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
‎የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራዎቻቸውን በእውነት፣ በሐቀኝነትና በታማኝነት ሊያከናውኑ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
‎በተቋማቱ የሚካሄዱ የሪፎርም አጀንዳዎች ዓላማ ዩኒቨርስቲዎች ካሉባቸው ተለምዷዊ የአሰራር ልምዶች በማላቀቅ አርአያነት ባለው መልኩ ተልዕኳቸውን እንዲፈጽሙ ማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ምልመላ የሚፈለጉ የአመራር ክህሎቶችን መሠረት ያደረገ ግልጽነትና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ፣ ከኢንዱስትሪና የውጭ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጭምር በሚጋብዝ መልኩ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል።
‎ለዩኒቨርስቲዎች የሚመደበው የጥቅል በጀት ስሌት በቀመር ላይ እንዲሁም በግልጽነትና ተጠያቂነት ላይ በተመሠረተ አኳሃን ሊፈጸም እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
‎በየደረጃው ያሉ የዩዩኒቨርስቲ አመራሮች ለሥራቸው የሚያግዛቸውን የአመራር ስልጠና በማግኘት የአመራር ክህሎት እንዲያጎለብቱ የስልጠና ማዕከል መቋቋሙንም አመላክተዋል።
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጣቸውን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንዲችሉ እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎የተዘጋጁት ደንብና መመሪያዎችም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ሥራዎቻቸውን በግልጸኝነትና ወጥ የሆነ አሰራር በማስፈን የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
‎ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ደንብና መመሪያዎቹ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በሙያቸው የሰለጠኑ ብቁና ችሎታ ያላቸው የትምህርት አመራሮችን ወደ ስራ ማስገባት እንደሚያስችሉም ገልጸዋል።
‎የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው በመድረኩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ፣ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ ደንብ ፣ ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
‎ውይይት የተደረገባቸው ሰነዶች ተቋማቱ ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት ሀብቶቻቸውን በአግባቡ በማስተዳደር ለታለመለት ዓላማ እንዲያውሉና የትምህርት ጥራት እንዲያስጠብቁ እንደሚያስችሉም አስረድተዋል።
‎በመድረኩ ላይ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
Recent News
Follow Us