News Detail

National News
Mar 19, 2026 31 views

ኢትዮጵያ እና ኒውዝላንድ በትምህርቱ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደርጉ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኒውዝላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ኦውንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ አካላት በትምህርት ዘርፉ የነበራቸውን ትብብር አጠናክረው መቀጥል በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ውቅት የትምህርት ሚኒስትሩ በትምህርት ሥርዓቱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትምህርት ዘርፉ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን ለአምባሳደሯ አብርራተውላቸዋል።

እነዚህን የሪፎርም ተግባራት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግም ከሀገሪቱ የመልማት ፍላጎት ጋር አብረው በሚሄዱ አዳዲስ የትምህርት መስኮች፣ በከፍተኛ ትምህርት ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ልማት፣ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ግብዓት አቅርቦትና በመሳሰሉት ላይ የአጋር አካላትን ድጋፍ እንደሚፈልጉ ጠይቀዋል።

 

በኢትዮጵያ የኒውዝላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ኦውን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ እየተገበረቻቸው ያሉ የሪፎርም ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን ገልጸው ኒውዝላድ በትምህርቱ ዘርፍ የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

በተለይም በነጻ የትምህርት እድል፣ በምሁራን ልውውጥ፣ በመምህራን ስልጠናዎች፣ በትምህርት ቤት ምገባ የእርሻ ልማት፣ የባህል ልውውጥና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ ለሚንስትሩ አብራርተውላቸዋል።

በስተመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች በትምህርቱ ዘርፍ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ ቀጣይ ውይይት ለማድርግና በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል።

 

Recent News
Follow Us