News Detail
Mar 01, 2026
18 views
የተረጋጋ ሀገር እንዲኖር በትምህርት ዘርፉ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ያስፈልጋል፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዳሰነች ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመረቁበት ወቅት በትምህርት አቅርቦት ረገድ በሁሉም አካባቢ ምንም ልዩነት ሊፈጠር አይገባም ብለዋል።
ይህንንም ለማረጋገጥም በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝም አብራርተዋል ።
በተለይም ምቹ የመማሪያ ከባቢን በሁሉም አካባቢ ለመፍጠር “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንና የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገና መደረጉን አንስተዋል።
አክለውም የትምህርት ስራ የሚለወጠው ከታች ጀምሮ ሲሰራ መሆኑን በማመን በከተማና በባለሀብቶች ብቻ ታጥሮ የቆየውን የቅድመ አንደኛ ትምህርት በመቀየር በሁሉም አካባቢ ያለ ልዩነት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ጠቅሰዋል።
በዚህም ባለፉት ዓመታት ከ34 ሺ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማና በገጠር ተገንብተው የአምስተና ስድስት ዓመት ህፃናት እየተማሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ትምህርት ለሁሉ ነገር ወሳኝ በመሆኑ ልጆቻችንን በአግባቡ በማስተማር የአለምን ፈተና መቋቋም የሚችሉ ጠንካራ ሀገር ተረካቢዎችን ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
አክለውም የትምህርት ሥራ ከፖለቲካ መላቀቅ አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ሁሉም ነገር ፖለቲካ መሆኑ ቀርቶ ትምህርት የሁላችን እንዲሆን በማድረግ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026