News Detail

National News
Feb 27, 2026 17 views

ኢትዮጵያ የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን '' አድዋ 130፣ ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል አገራዊ መሪ ቃል አክብረዋል።
‎የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ህያው ተምሳሌት በመሆኑ አባቶቻችንና እናቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነትና ላጎናጸፉን ድል ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
‎ትምህርት ለምናደርገው የእድገትና የብልጽግና ጉዞ ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ጅምር ስራዎቻችንን አልቆ በመፈጸም እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትር ደኤታ አስገንዝበዋል።
‎አገራችን ለዜጎቿ የተመቸችና የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ የትምህርት ዘርፉ ተዋናዮች የበኩላቸውን ድርሻ በላቀ የአገር ፍቅርና ስሜት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ክብርት ወ/ሮ አየለች አንስተዋል።
‎የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከመሠረቱ በህጻናት ላይ መስራት የሚገባን መሆኑን በመረዳት ለህጻት ትምህርት የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
‎ዳር ድንበሮቻችንን ለመጠበቅና ማህበራዊ እሴቶቻችንን ለማዝለቅ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚገባም ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል።
‎የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው ለአንድነታችንና ለብሔራዊ ጥቅማችን ባለው ፋይዳ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የክብረ በዓሉ ዓላማ መሆኑን አስተው አድዋ በዓለም ታሪክ አፍሪካዊት አገር ቅኝ ግዛትን በጦር ኃይል ያሸነፈችበትና በደማቅ ቀለም የተጻፈ ታሪካዊ ተምሳሌት የሆነችበት አኩሪ ታሪክ መሆኑን ጠቅሰዋል።
‎በክብረ በዓሉ ላይ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ አቶ ዑመር ይማም በበኩላቸው የአድዋ ድል ብሔራዊ የአንድነትና የአሸናፊነት ምልክት መሆኑን አስረድተዋል።
‎የብሄራዊ ጥቅም የመጀመሪያው መነሻ ሉዓላዊነት በመሆኑ በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ ዜጎች በአንድነት ሊቆሙ እንደሚገባም ገልጸዋል።
‎በክብረ በዓሉ ላይ በተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች ቀርበው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
Recent News
Follow Us