News Detail

National News
Jan 23, 2026 19 views

ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፤

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
‎ መምህራን በስርዓተ ትምህርቱ መሠረት ስለሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል ለአቅም ማጎልበት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም ጠቁመዋል።
‎የትምህርት ቤቶች ግብዓቶችን ከማሟላት አንጻር በተለይም በራስ አቅም መሟላት የሚችሉ የትምህርት መርጃ ግብዓቶችን በአግባቡ ለማሟላት የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም አቶ ሱልጣን አስረድተዋል።
‎በከተማ አሰተዳደሩ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብርም ተጨማሪ የመምህራን ማረፊያዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተሙከራዎች፣ ቤተመጽሐፍቶች የመገንባትና የማደራጀት ስራዎች መከናወናቸውንም ተናግረዋል።
‎ትምህርት ቤቶችን ሳቢ፣ ውብና ማራኪ በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ሆነው ተማሪዎችና መምህራን በናፍቆት የሚመጡባቸው ስፍራዎች ለማድረግ የትምህርት ቤት ምድረ ግቢዎችን የማስተካከል ስራዎች መሰራታቸውንም ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል።
‎‎በአስተዳደሩ የትምህርት ጥራት ጠንቅ የሆነውንና ከስነምግባር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለማስወገድ ወላጆች ከትምህርት ቤቶች ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም አቶ ሱልጣን አስታውቀዋል።
‎በአስተዳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በተሻለ መልኩ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው በዚህ ዓመትም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
Recent News
Follow Us