News Detail

National News
Feb 25, 2025 39 views

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ የማድረግ ሂደት የሁሉንም ባለድርሻዎች ድጋፍና ትብብር እንደሚጠይቅ ተጠቆመ፤

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ አስተዳደር ስትራተጂክ እቅድ እና ሴኔት ህግ ለማዳበር የተዘጋጀ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አውደ ጥናቱን ሲከፍቱ እንደገለጹትት የዩኒቨርስቲዎችን የራስ ገዝ አስተዳደር ማስፋት የመንግስት አካላት ፣ የአካዳሚክ መሪዎች፣ የመምህራን ፣የተማሪዎችና የማህብረሰቡን ትብብር ይሻል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ -ገዝነት የተቋማቱን ራስን በራስ የማስተዳደርና አካዳሚያዊ ነጻነትን በማረጋገጥ የትምህርት ጥራት ምርምርና ፈጠራን በውጤታማነትና በብቃት ለመፈጸም እንደሚያስችል ክቡር አቶ ኮራ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር በላይ ካሳ በበኩላቸው የአውደ ጥናቱ ዓላማ ወደ ራስገዝነት ሽግግር ለሚያርጉ የመንግስት ዩኒቨርሰቲዎች ወሳኝ የሆኑ ስትራቴጂክ እቅድና ሴኔት ህግ ለማዳበር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አውደ ጥናቱ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን ለመደገፍ የአሜሪካ መንግስት ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ፕሮፌሰር በላይ አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው ድጋፉ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግስታት መካከል ያለው ድጋፍና ትብብር አካል መሆኑን ተናግረዋል፡
በኢትዮጵና በአሜሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከከል የቆዬ የአካዳሚክና ምርምር ልውውጥ መኖሩን የጠቆሙት አምባሳደሩ ያሁኑ ድጋፍ ዘጠኝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርጉትን ሂደት እንደሚያግዝም ጠቅሰዋል።
የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ በበኩላቸው ዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የመቀሌ፣ የጎንደር ፣ የባህርዳር፣ የአዲስ አበባ ሳንስና ቴክኖሎጂ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የሀዋሳ ፣ የጅማ፣ የሐረማያ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶችና የሚመለከታቸው ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
Recent News
Follow Us